Thursday, January 9, 2014

ሰማያዊ ፓርቲ ሀሳቡን በኢሳት ላይ ለመግለጽ የማንንም ይሁንታ እንደማይጠይቅ አስታወቀ

http://ethsat.com/amharic
ታህሳስ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው ” የምንናገርበትን የመገናኛ ብዙሃን ማንም እንዲመርጥልን ወይም እንዲወስንልን አንፈቅድም” በሚል ርእስ ባወጣው የአቋም መግለጫ፣ ” ሰማያዊ ፓርቲ መልዕክቱን የሚያስተላልፍበትን መገናኛ ብዙሃን ማንም አካል እንዲመርጥለት ወይም እንዲወስንለት የማይፈልግ መሆኑን ግልፅ ” አድርጓል።
“በሕገ መንግስቱ የተረጋገጠውን ማንም ሰው በመረጠው መንገድ ሃሳቡን የማስተላለፍ መብቱን በመጠቀም በኢሳትም ሆነ እድሉን ካገኘ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አቋሙንና እምነቱን ማስተላለፍ የሚቀጥል መሆኑን ማረጋገጥ ይወዳል” በማለት ፓርቲው በኢሳት ላይ ቀርቦ አቋሙን ከመግለጽ እንደማይገታ ግልጽ አድርጓል።
ሰማያዊ ፓርቲ ታህሳስ 25 ቀን 2006 ዓም በኢቲቪ የተላላፈውን ዶክመንታሪ ፊልም “የእብሪት መልዕክት” ያዘለና እና “ከተራ ርካሽ ፕሮፓጋንዳነት የማያልፍ የሕግና የዲሞክራሲያዊ መብት ገደብን ካለማወቅ የሚመነጭ አስተሳሰብ ነው” ሲል አጣጥሎታል።
“የብሔራዊ ደህንነት መረጃ እና የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል  በተደጋጋሚ ጊዜ በሽብር ወንጀል ጠርጥሬአቸዋለሁ የሚላቸውን ሁሉ በመክሰስ ወደ እስር ቤት እንዲወርዱ እያደረገ ጉዳያቸው የፍርድ ቤት ውሳኔ ሳያገኝ እንደፈለገ በሚቆጣጠረው ወይም በሚያዘው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት አማካኝነት የፈለገውን ዓይነት ፍረጃና ሥም ማጥፋት ሲያካሒድባቸው” መቆየቱን ያስታወሰው ሰማያዊ ፓርቲ፣ ይህ ራሱን ከሕግ በላይ የሰቀለ አካል ያለምንም ገደብ ከሚሰራቸው ተግባራት እንዲታቀብ በሕግ የሚያስቆመው በመጥፋቱ እስካሁን የፈፀማቸውን የማንአለብኝነት ተግባራት እንደጥፋት ሳይሆን እንደ መልካም ሥራ ቆጥሯቸው በተመሳሳይ የሥም ማጥፋትና የፍረጃ ተግባሩ እንዲገፋበት አድርጎታል” ብሎአል።
“ኢሳት” የተባለ የመገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ መንግስት በሽብርተኝነት ከተፈረጀ ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ እንደተደረገለትና በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች በተለይም ሰማያዊ ፓርቲ በዚህ የመገናኛ ብዙሃን እንዳይጠቀም የማስጠንቀቂያ ዛቻ ተላልፎለታል” ሲል ያስታወሰው ሰማያዊ ፓርቲ፣  ይህ አስፈራሪ አካል ራሱን ሕግ አውጭና ሕግ ተርጓሚ በማድረግ የዚህች ሐገር ዜጎች ሃሳባቸውን የሚገልጹበትንና የማይገልጹበትን የመገናኛ ብዙሃን እየወሰነላቸውና እየመረጠላቸው ይገኛል፣ ብሎአል ።
የገዥው ቡድን ሰዎች ሀሳብን በሃሳብ ማሸነፍ እንደማይችሉ ስለሚያውቁት የቀራቸው አማራጭ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ሃሳባቸውን የሚያሰራጩባቸውን መንገዶች መዝጋት ብቻ መሆኑን ፓርቲያችን ይገነዘባል ያለው ሰማያዊ ፓርቲ፣  ማንም አካል በሕግም ሆነ በሞራል ተጠያቂ የሚሆነው የሚያስተላልፈው መልዕክት ይዘት የሌሎችን ዲሞክራሲያዊና ሞራላዊ መብት የሚጋፋ መሆን አለመሆኑ እንጂ ገዥው ቡድን በጠላው ወይም በወደደው የመገናኛ ብዙሃን መልዕክቱን ማስተላለፉ አይደለም” ሲል አቋሙን ግልጽ አድርጓል፡፡ መልዕክትን የገዥው ቡድን ሰዎች በጠሉት የመገናኛ ብዙሃን ማስተላለፍ በራሱ ወንጀለኛ ወይም ሽብርተኛ ለማድረግ የሚያበቃ ምንም ዓይነት የሕግ መሰረት እንደሌለውም ገልጿል፡፡
ፓርቲው በመጨረሻም ” ሰማያዊ ፓርቲ መልዕክቱን የሚያስተላልፍበትን መገናኛ ብዙሃን ማንም አካል እንዲመርጥለት ወይም በዚሁ አጋጣሚም የፓርቲያችንን መልካም ስም በሃሰት ለማጉደፍ የተሰነዘሩ ቃላትን በቀላሉ የማንመለከታቸው መሆኑን ሕግ ባለበት ሐገር ራስን ከሕግ በላይ በማስቀመጥ ማንንም አካል መፈረጅና ስም ማጉደፍ በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑን የዘጋቢ ፊልሙ ባለቤቶች እንዲያውቁትና ወደፊትም ተመሳሳይ ድርጊት ከመፈፀም እንዲቆጠቡ እናሳስባለን፡፡” ብሎአል።
በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱት ሰማያዊ ፓርቲ እና አንድነት ፓርቲ በኢሳት ላይ ቀርበው አቋማቸውን እንዳይገልጹ መንግስት ሰሞኑን ምክር አዘል ማስጠንቀቂያና ማስፈራሪያ በኢቲቪ አማካኝነት መስጠቱ ይታወሳል።
ከመጪው ምርጫ ጋር ተያይዞ ኢሳት ገዢውን ፓርቲ ጨምሮ በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ፕሮግራሞቻቸውንና መልእክቶቻቸውን በነጻ እና ያለገደብ የሚያስተላልፉበትን አሰራር በመቀየስ ላይ ነው።

Wednesday, January 8, 2014

አንድነት – አቶ አለማየሁ ለሴቦ፣ የአንድነት ፓርቲ አባል በሲዳማ ታሰሩ





https://www.andinet.org

አቶ አለማየሁ ለፌቦ የተባሉ የአንድነት ፓርቲ አባል፣ ከፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ማግስት ወደ ክልሉ ሲመለሱ እንደተያዙ ለማወቅ ተችሏል። ፖሊሶቹ እንደ ክስ ያቀረቡት ነገር፣ «የፓርቲውን ሰነድ በወረቀትና በኮምፒዩተርህ ውስጥ ተገኝቷል» የሚል እንደሆነ ለማወቅ ችለናል፡፡ አቶ አለማየሁ በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው፣ ህጋዊ በሆነ ፓርቲ መሳተፉቸውና ስብሰባ ላይ መገኘታቸው ምን ዓይነት ወንጀል እንደሆነ ለማጣራት ወደ ሌንሳቦ ወረዳ ወርቃ ከተማ ብንደውልም አስተያየት የሚሰጠንን አላገኘንም፡፡
እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት ማንም ሰው በየትኛው ህጋ ድርጅት ውስጥ መሳተፍና መጀራጀት እንደሚችል፣ የሀሳብ ነፃነት እንዳለው፣ ያንንም ማንፀባረቅ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡ እየሆነ ያለውና በአቶ አለማየሁን ለእስር ያበቃው ግን እጅግ ከዚህ ጋር የሚጋጭ ነው፡፡ አቶ አለማየሁ በአሁኑ ሰዓት በዕስር ላይ የሚገኙ ሲሆን ተጨማሪ መረጃ እየተከታተልን እናቀርብሎታለን፡

አንድነት ፓርቲ ለሚዲያዎች ሃሳብን መግለጽ አሸባሪነት አይደለም አለ

ታህሳስ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ሰሞኑን ኢቲቪ ባዘጋጀው ዶክመንተሪ ላይ “መቀመጫውን በውጭ በማድረግ የተለያዩ ዜናዎችንና ፕሮግራሞችን በማሰራጨት የሚታወቀውን ኢሳት(ESAT) ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ፓርቲያችን ለአባላቱ እና ለደጋፊዎቹ መልዕክት ማስተላለፉን እንዲሁም እንደፓርቲ ለማንኛውም ሚዲያ የፓርቲያችንን ሰላማዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ ስንጠየቅ የመመለስ መብታችንን በሚጋፋ መልኩ የፓርቲያችንን አቋም አዛብቶ ለማቅረብ ሞክሯል” ብሎአል፡፡
“ኢህአዴግ በሚጠላቸው እና በሚያጥላላቸው ሚዲያዎች ሃሳብን መግለፅ በየትኛውም መመዘኛ አሸባሪነት ሊሆን አይችልም” ያለው አንድነት፣  የኢህአዴግ መንግስት ሲያስነጥሰው ከሚያለቅሱለት የፕሮፓጋንዳው ፍጆታዎች ከሆኑት ሚዲያዎች ውጪ የኔ ያልሆኑ የሌላ ናቸው ብሎ የሚያምን በመሆኑም ፍረጃው ህጋዊ አግባብነትም ሆነ መረጃ የሌለው ባዶ ፍረጃ ” ነው በማለት የመንግስትን ማስጠንቀቂያ አጣጥሎታል።
“ኢህአዴግን  የህዝብን ጥያቄ በዶክመንተሪ ጋጋታ መመለስ እንደማይቻል” ልናስታውሰው ብንሞክርም፣  አሁንም በዶክመንተሪ ፊልሞች ስም ከማጥፋት፣ ከመፈረጅና ከማስፈራራት መላቀቅ አልቻለም፡፡ ” ሲል ፓርቲው አክሎ ገልጿል።
አንደነት በመጨረሻም ” ህገ መንግስታዊ መሰረት የሌለው ቢሆንም እንኳ ቢያንስ ራሳቸው ላወጡት ህግ ታምነው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ ሳያስወስኑ አንድን የሚዲያ ተቋም ያውም ለአንድ አላማ የተቋቋመ የፀረ-ሽብር ግብረሃይል ‹‹የአሸባሪ ድርጅት ልሳን ነው›› ወይም ‹‹አሸባሪ ነው›› በማለት ሲፈርጅ ስናይ አሁንም የሀገራችን ፖለቲካ ፓርቲና መንግስት የተደበላለቁበት፣ አንድ ድርጅት እንደፈለገው የሚፈርጅበት ስርዓት እንዳለ የሚጠቁም ነው” ብሎአል፡፡

People think Ayalew resigned due to reasons related to Border issue, Gov’t study finds

ESAT News
January 7, 2014
A new study conducted by the Public Opinion Information Section of the Government Communication Affairs Office has found that the resignation of Ayalew Gobeze, the ex-president of the Amhara Regional State, is a strategy by the government to better carry out the border demarcation between Tigray and Amhara regions.  Ayalew Gobeze resigned from his post last month and was succeeded by his Deputy Degu Andargachew in what the government called a ‘power succession’.
According to the information collected Degu Andargachew is not well received by the populace. Many believe that he is only there to execute the plans and demands of the Tigrean People’s Liberation Front (TPLF).
Similarly, Ahmed Abetew, former Deputy Administrator and currently Ethiopia’s Trade Minister, and Alemnew Mekonen, Head of the Amhara National Democratic Movement (ANDM) Secretariat are both labelled as loyal to the TPLF. Insiders told ESAT that the two officials have been discovered possessing two Eurotracker vehicles; they have not been removed from their positions due to their loyalty to the TPLF.
During a cabinet evaluation, the two officials had said that the two vehicles were given to them by Chinese Companies in consideration of their ‘leadership qualities’. According to the Office there was no opinion given ‘benignly’. The opinions will presented to the Government’s Information Section and the Cabinet will discuss on it.

Monday, January 6, 2014

የቴዲ አፍሮ ኮካኮላ ውል እንዲሰረዝ ዘመቻ ተጀመረ

 http://ecadforum.com/Amharic/archives/10659/
January 6, 2014

ኢትዮጵያውያን ዝምታውን በመስበር የሶሻል ሚድያ ዘመቻ መክፈት ይገባቸዋል

በ2014 ብራዚል ለሚካሄደው የአለም ዋንጫ ላይ ቴዲ አፍሮ የክብር እንግዳ እንዳይሆን አዲስ ዘመቻ በእነ ጃዋር መሃመድ መጀመሩ ተሰማ።Coca-cola a global leader in the beverage industry
በዓለም ዙርያ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ ለተፈናቀሉ ወገኖች እየተረባረቡ ባሉበት በዚህ ፈታኝ ወቅት፤ ጃዋር እና ሜንጫዎቹ ጸረ-ኢትዮጵያዊነት ዘመቻቸውን በስፋት ተያይዘውታል። በዛሬው እለት ከአዲስ አበባ በደረሰን ዜና መሰረት ኮካኮላ የቴዲ አፍሮን የአለም ስፖርት ፌዴሬሽን (ፊፋ) ስፖንሰርነት እንዲያነሳ ጠይቀዋል። አዲስ አድማ ለመጀመርም ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል።
በ2014 ብራዚል ለሚካሄደው የአለም እግር ኳስ ዋንጫ አፍሪካን ወክሎ እንዲገኝ ኮካኮላ ቴዲን የመረጠው መሆኑ ይታወሳል። የአለም ስፖርት ፌዴሬሽን (ፊፋ) ወጣቱ ቴዲ አፍሮ አፍሪካን እንዲወክል መምረጡ ዘረኞቹን አስቆጥቶ እንደነበር የሚታወስ ነው።
ቴዲ አፍሮ በአለም መድረክ ላይ የሚያቀርበው ኢትዮጵያዊ የሙዚቃ ቃና ሀገራችንን እና መላው አፍሪካን የሚያስጠራ ነው።
የሄነከኑ አድማ በኦህዴድ ብርቱ ጥረት የተሳካላቸው እነኚህ ባለ አድማዎች፣ ሰሞኑን የደስታ መግለጫቸውን በየድረ-ገጾቻቸው ላይ እየተለዋወጡ እንደሆነ ተገልጿል። ሄኒከን ኮንሰርቱን የሰረዘው ከኦህዴድ በተላለፈ ቀጭን ትእዛዝ ስለመሆኑ ማስረጃው አሉ።
እነ ጃዋር በዚህ አላበቁም። በዲሴምበር 8፤ 2013 በተላለፈ የአቶ ቡልቻ ደመቅሳ እና ሌሎች ምሁራን ቃለ-ምልልስ ምክንያት የጀርመኑ (ዶቸ ቨለ) የአማርኛ ድምጽ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ከስራ እንዲነሳም ከአቤቱታ ጋር ቀጭን ትእዛዝ ለቦርዱ አስተላልፎ ነበር። የዶቸ ቨለ ቦርድ ላይ ኦህዴድ ተጽእኖ ስለሌለው ይህ ዘማቻ ሊሳካ አልቻለም።
የኮካኮላው ዘመቻ የተነጣጠረው በቴዲ አፍሮ ላይ ሳይሆን በአኢትዮጵያዊነት ላይ ስለሆነ በአለም ዙርያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ዝምታውን በመስበር በነዚህ ሰዎች ላይ የሶሻል ሚድያ ዘመቻ መክፈት ይገባቸዋል።

በምነው ሸዋ ኢንቴርቴንመንት አማካኝነት ወደ አሜሪካ የመጣው ሀንቻሱ ሁንዴሳ የተባለው ዘፋኝ በሚካሄዱት ኮንሰርቶች ላይ ከፍተኛ ጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻ ከፍትዋል

 http://www.boletoday.com/shewa/
በምነው ሸዋ ኢንቴርቴንመንት አማካኝነት ወደ አሜሪካ የመጣው ሀንቻሱ ከፍተኛ የኢትዮጵያ ጥላቻ ያላቸው ያለው ግለሰብ ከመሆኑም በላይ አማርኛን ማውራት የማይወድና ሌሎችን ኢትዮጵያውያን በተለይም አማራውን በከፍተኛ ጥላቻ የሚያይ ነው ::በቅርቡ በየስቴቱ በተካሄደው ኮንሰርት ላይ ይህንን ጥላቻ የሚያሳዩ ጥላቻን ሚዘሩና እልቂትን ሚጋብዙ ዘፈኖችን ሲጫውት  በተደጋጋሚ ታይትዋል:: የምነው ሸዋ ባለቤት ዝምታን የመረጠው ኦሮሞ ስለሆነ ወይስ ጉዳዩን ስላላወቀ እንደሆነ ለማወቅ አልተቻለም::

hqdefault-1

mqdefault

Sunday, January 5, 2014

የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር! ኢቲቪ ስለ ኢሳት


http://ecadforum.com/Amharic/archives/10645/
January 4, 2014
ቢታኒያ አለማየሁ፣ አዲስ አበባ

ዶክመንታሪ ብሎ ዝም! አስቡት እስኪ ኢህአዴግን በሚያክል አፋኝ መንግስት በኢቲቪ ኢሳት ሲብጠለጠል፣’ኢሳት ማለት የኢትዮጵያ ህይዝብ እውነተኛ የመረጃ ወፍጮ ነው!’Ethiopian Satellite Television (ESAT)

ለምን ግን በዚህ ሰአት ስለ ኢሳት ዶክመንታሪ መስራት አስፈለገ?
-ኢሳት ከተመሰረተ አንስቶ እስካሁን ድረስ በእውነተኛ መረጃ ምንጭነት በመላው የኢትዮጵያ አንጀት ውስጥ ተደላድሎ መቀመጡን ስልሚያውቁ!
-ይከስማል ይጠፋል አቅሙ ይዳከማል ሲሉት እንደ ወይን ጠጅ ከለት እለት እየበሰለና እየጎመራ መምጣቱን ስላዩ!
-በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ተምልካቾች ለኢሳት በመደወል በሚሰጡት አስተያየት ህዝቡ በሚገባ እየተከታተለው መሆኑን ስላረጋገጡ!
-ከዚህ ቀደም ከሰባት ጊዜ በላይ ጃም በማደርግ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርገውን ስርጭት ቢያቛርጡም ኢሳት ግን የተለያዩ የሳተላይት አማራጮችን በመጠቀም ከአንድ አመት በላይ(እስካሁን) ያለ ምንም ችግር ወደ ኢትዮጵያ ማሰራጨ ስለቻለና አሁን ካለው የኢኮኖሚ ሁኔታ አንጻር ጃም ማድረግ ከፍተኛ ወጪ ስለሚጠይቅ!
-ህዝብን አደንቁሮ በኢቲቪ ፕሮፓጋንዳ ብቻ የህዝብን አምሮ ለማደደብ በሚደርገው ጥረት ኢሳት ነጻ ሃሳብ በማነሸራሸር እንቅፋት ስለሆነ!
ባጠቃላይ ኢሳት ለህዝብ እውነትን በመግለጽ ለስረአቱ የእግር እሳት መሆኑ ስለታመነበት:- የኢሳትን ይዘት ተንትኖ እና እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ኢሳት ግን እንዲህ ይላል በሚል አመክኖዋዊ አስተሳሰብ ከመሞገት ይልቅ፣ ግንቦት ሰባት አሸባሪነው ኢሳት ደግሞ የግንቦት ሰባት ነው ስለዚህ ኢሳት አሸባሪ ነው ብለው ከደመደሙ በኋላ ህዝቡ አሳትን መከታተል እንደ ሽብርትኛነት አድርጎ ቆጥሮት መከታተሉን እንዲያቆም ለማግባባት ቀጥሎም ለማስገደድ ያመች ዘንድ የተሰራ ድራማ ነው! የዘፈን ዳር ዳሩ እስክሳ ነው ትል ነበር አያቴ! የሚገርመው ግን አቶ ሃይለማሪያም እንዳሉት “ግንቦት ሰባት በቅዠትላይ የተመሰረተ ድርጅት” ከሆነ ይህን ያክል ተከታታይ ድራማዎች በመስራት ምን አደከማቸው? በራሱ ጊዜ ከእንቅሉ ይባንንላቸው የለም እንዴ?
እናንት አሸባሪ ኢሳቶች ሆይ ህዝብን እልል እያስባላችሁ አንባገነኖችን እያሸበራችሁ ነውና በርቱ! በርቱ! በርቱ!
ቢታኒያ አለማየሁ