Wednesday, December 25, 2013
ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤቱን እንዲለቅ ትእዛዝና ማስጠንቀቂያ ተሰጠው::
ታህሳስ ፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰማያዊ ፓርቲ ግንፍሌ አከባቢ የሚገኘውን እና በጽ/ቤትነት የሚጠቀምበትን ቢሮ በአስቸኳይ እንዲለቅ ትዕዛዝ ደረሰው።
በዛሬው እለት ከሰኣት በኋላ አቶ ሄኖክ የተባሉ አከራዩ ከአራት ግለሰቦች ጋር በመምጣት ፦”ቤቱን ለነዚህ ግለሰቦች ስለሸጥኩላቸው እንድትለቁላቸው” ሲሉ ከውል ውጪ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
ቤቱን ገዛሁት የሚለው ግለሰብ በበኩሉ፦”ቤቱን የኔ ስለሆነ በአስቸኳይ እንድትለቁልኝ፣ ካልሆነ የራሴን እርምጃ እወስዳለሁ” ሲል አመራሮቹ ላይ ዝቷል::
ይህ ግለሰብ በማይመለከተው ጉዳይ በመግባት፦” ከዚህ በፊትም ልቀቁ ተብላችሁ በተደጋጋሚ እንደተነገራችሁ መረጃው አለኝ፤ በቶሎ የማትለቁ ከሆነ እርምጃ ይወሰድባችሁዋል” በማለት በአመራሮቹ ላይ ቁጣ የተቀላቀለበት ዛቻ በመዛት ሄዷል:;
ሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ ቀደም በመነን አከባቢ ተከራይቶት የነበረውን ጽ/ቤት ገና ሳይገባበት በዝግጅት ላይ እንዳለ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና እና ቅጥረኞች በተቀናጀ አፈናና ሀይል የተቀላቀለበት እርምጃ ቢሮውን እንዳስለቀቁት ይታወቃል::
ቀደም ሲል ከሰማያዊ ፓርቲ የተነጠቀውን ቢሮ የወሰደው ካድሬም፤ ፔንሲዎን ከፍቶ እየነገደበት እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ ፓርቲያቸውን በውጪ አገራት ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በማስተዋወቅ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።
ሰበር ዜና]አርቲስት ሚኪያ በሀይሉ አረፈች Artist Mikaya Behailu has passed away
December 25, 2013
download (1)
ድምፃዊ ሚኪያ ባሃይሉ አረፈች !! ሰሞኑን በጨጓራ ህመም ስትሰቃይ እንደነበር እና የሞቷም መንስኤ ይሄው ህመም መሆኑን ምንጮች ገልፀዋል ፡፡ ሚኪያ በመምህርነት ሙያ ያገለገለች በኋላም ወደሙዚቃ በመግባት ሸማመተው በሚል አልበሟ ከፍተኛ እውቅና አግኝታ ያገኘች ወጣት አርቲስት ነበረች ፡፡
ለአድናቂወቿና ለቤተሰቦቿ
Tuesday, December 24, 2013
በቀብሪ ቤያህ እስር ቤት ውስጥ የሞቱ ሰዎች የሉም ሲል የክልሉ ፖሊስ አዛዥ አስተባበሉ
http://ethsat.com/amharic

ታህሳስ ፲፫( አስራ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ
ጽህፈት ቤት ፖሊስ አዛዥ ከጅጅጋ 25 ኪሜ ገደማ በምትገኘዋ ቀብሪበያህ እስር ቤት ውስጥ የሞቱ ሰዎች
ስለመኖራቸው ሪፖርት እንዳልደረሰቻው ገልጸዋል። አዛዡ እንዳሉት በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ሽብረተኞችን በተመለከተ
ከፌደራል መንገስቱ የጸረ ሽብር ግብረሀይል ጋር በጋራ የሚሰሩ በመሆኑ፣ በዚሁ ወንጀል ተጠርጥረው የሚያዙ ካሉ በጋራ
የሚታይ ጉዳይ ይሆናል ሲሉ አክለዋል
በጅጅጋ የተከበረውን የብሄር ብሄረሰቦች በአል ምክንያት በማድረግ “መታወቂያ የላቸውም፣ የከተማዋን ገጽታ ያበላሻሉ፣ ከተማዋን ያቆሽሻሉ፣ የጸጥታ ስጋት ደቅነዋል በሚል ከ770 በላይ ሰዎች ቀብሪበያህ በሚባለው ወረዳ ውስጥ በአንድ ክፍል ውስጥ እንዲታሰሩ ከተደረጉት መካከል ከ40 በላይ የሚሆኑት መሞታቸውን ማንነታቸው እንዳይታገለጽ ከጠየቁ የክልሉ ባለስልጣናት ያገኘውን መረጃ በመንተራስ ዘገባ መስራታችን ይታወሳል።
እስረኞቹ የሞቱት በምግብ እጥረትና በእስር ቤቱ ውስጥ በተነሳ የታይፎይድ ( ተስቦ) በሽታ መሆኑን የዜናው ምንጮች ገልጸዋል። ዘመዶች የሞቱባቸውንና ለቅሶ የተቀመጡ ሰዎችን ኢሳት ለማነጋገር ቢሞክርም፣ ሰዎቹ ለደህንነታቸው በመስጋት ለመናገር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
ሰዎችን ከከተሞች በመውሰድ ያሰሩዋቸው በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱት ልዩ ሚሊሺያ እየተባሉ የሚጠሩት ታጣቂዎች መሆናቸውን ምንጮች አክለው ገልጸዋል። ማንኛውም የሰብአዊ መብት ድርጅት በአካባቢው በመሄድ በቀላሉ ማረጋገጥ የሚችለው ሀቅ ነው በማለት የክልሉ ፖሊስ አዛዥ የሰጡትን ማስተባበያ ውድቅ አድርገዋል። ለሁለት ወራት ያክል ታስረው የነበሩት በተለያዩ ምክንያቶች የታሰሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ባለፈው ሳምንት መለቀቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

Sunday, December 22, 2013
ወታደራዊ መኮንኖች የደሞዝ ይጨመርልን ጥያቄ አቀረቡ
ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ካለፉት 8 ቀናት ጀምሮ ስብሰባ ላይ ሲሆኑ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ዋነኛው የመነጋገሪያ አጀንዳ መሆኑ ታውቋል።
ከመቶ
አለቃ በላይ ማእረግ ያላቸው ወታደራዊ መኮንኖች ስብሰባዎችን እያካሄዱ ያሉት የጄኔራሎች ስብሰባ ከወር በፊት
መጠናቀቁን ተከትሎ ነው። በጄኔራሎቹ ስብሰባ ላይ ለሰራዊቱ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ተነስቶ የነበረ ቢሆንም፣ “ሰራዊቱ
አሁን የሚያገኘው ደሞዝ ለኑሮው በቂ ነው” የሚል መልስ ከሰራዊቱ ዋና አዛዦች ተሰጥቷል። በተሰጠው መልስ
የተበሳጩት ጄኔራል ሰአረ መኮንን ስብሰባ ረግጠው ወጥተው እንደነበር ታውቋል። ጄኔራሉን ለማረጋጋት ከፍተኛ ጥረት
ተደርጎ እንደነበርም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ጄኔራል ሰአረ ለሰራዊቱ ደሞዝ እንዲጨመር አቋም ከያዙት ከፍተኛ
መኮንኖች መካከል አንዱ ናቸው።
ሰሞኑን በመካሄድ ላይ ባለው ከጄኔራል በታች ማእረግ ባላቸው መኮንኖች ስብሰባም የደሞዝ ጭማሪና የኑሮ ውድነት ዋና አጅንዳ ሆኖ ቀርቧል።
በምስራቅ አካባቢ ባለው እዝ አንዳንድ መኮንኖች ” እኛ ቤተሰቦቻችንን ምግብ አብልተን ለማኖር አልቻልንም፣ እናንተ በሙስና በዘረፋችሁት ገንዘብ ልጆቻችሁን ውጭ አገር ልካችሁ ታስተምራላችሁ” በሚል አለቆቻቸውን በድፍረት መተቸታቸውን የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል። መኮንኖች ያቀረቡትን ጥያቄ የመደረክ መሪዎች ለመመለስ ሲቸገሩ ታይቷል።
መኮንኖቹ ስብሰባቸውን ሲጨርሱ ከተራ ወታደሮች ጋር የሚደረገው ስብሰባ ይቀጥላል ተብሎአል።
ከፍተኛ ቅሬታ እየተስተናገደበት ባለው ስብሰባ፣ ወታደሮቹ እንደ መኮንኖቹ ሁሉ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ሊያነሱ ይችላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ወታደራዊ ምንጮች ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አንድ ሻምበል የወለደውን ልጅ በእሳት ማቃጠሉ ታውቋል። በምስራቅ እዝ የሚገኘው ሻምበል ፈቃዱ በዳዳ ከሳምንታት በፊት በልጁ ላይ ቤንዜን በማርከፍከፍ ያቃጠለው ሲሆን፣ ልጁም ወዲያውኑ ህይወቱ ሲያልፍ አባቱ ደግሞ ቆስሎ ሆስፒታል ተኝቷል። ሻምበል ፈቃዱ በልጁ ላይ ይህን አሰቃቂ እርምጃ ለምን እንደወሰደ አልታወቀም።
http://www.clickhabesh.com/?p=103432

Friday, December 20, 2013
በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለማስወጣት የሚደረግ እንቅስቃሴ የለም ተባለ
http://ethsat.com/amharic
ታህሳስ ፲( አስር )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ሱዳን የተነሳውን የእርስ በርስ ግጭት ተከትሎ በአገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የደህንነታቸው ሁኔታ አሳሳቢ ቢሆንም መንግስት እስካሁን እርምጃ እየወሰደ አለመሆኑ ታወቀ።
የኢሳት የጁባ ወኪል እንደገለጹት አብዛኛው አገሮች ዜጎቻቻውን እያወጡ ነው ። ኬንያና ኡጋንዳ አውቶቡሶችን በመላክ ፣ አሜሪካና እንግሊዝ ደግሞ ወታደራዊ አውሮፕላኖችን በመላክ ዜጎቻቻውን እያወጡ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን ጁባ ማረፉን ተከትሎ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ለመመለስ ተስፋ አድርገው የነበረ ቢሆንም፣ አውሮፕላኑ ግን ቻይናዎችን ብቻ ጭኖ መመለሱ ታውቋል። ኢሳት ከአየር መንገዱ ለማረጋገጥ እንደቻለው የቻይና መንግስት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ቻርተር አውሮፕላን በመከራየት በነዳጅ ማውጣት ስራ ላይ የተሰማሩ ዜጎቹን ወስዷል።
እንዲሁም ለሽምግልና ጁባ የሄዱትን የኢትዮጵያን ባለስልጣናት በማሳፈር ጁባ ያረፈ አንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን፣ ባለስልጣኖችን ካወረደ በሁዋላ ትኬት ቆርጠው ለመውጣት ይጠባበቁ የነበሩ ኢትዮጵያውያንን ሳይጭን ባዶውን ተመልሷል። ኢትዮጵያውያኑ የኬንያንና የኡጋንዳን አየር መንገዶችን ለመጠቀም ጥረት እያደረጉ ቢሆንም፣ አየር መንገዶቹ ከፍተኛ ዋጋ በመጠየቃቸው ትኬቶችን ለመግዛት አልቻሉም።
ኢሳት ለማረጋገጥ ባይችልም ሶሰት ኢትዮጵያውያን ሴቶች መደፈራቸውን የሚያመለክት ዜና ደርሶታል። አንዳንድ ኢትዮጵያውያንም ንብረታቸውን ተዘርፈው በጁባ መንገዶች ላይ ያለ ደጋፊ ሲዞሩ እንደሚታይ ወኪላችን ገልጿል።
የኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ጅቡቲ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ላለፉት ሁለት ቀናት በጁባ ተገኝተው ሁለቱን ሀይሎች ለመሸምገል ጥረት እያደረጉ መሆኑም ታውቋል። ደ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ሁለቱንም ሀይሎች ለማቀራረብ ከፕሬዚዳንቱ ጥሩ ምላሽ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
ቦር የተባለው አካባቢ በአማጽያን እጅ የወደቀ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ድንበር በሆነው አኮቦ በትናንትናው እለት ጦርነት ተከፍቷል። ዛሬ ደግሞ ማላኪ፣ ዋው እና ባንቲዩ በተባሉት አካባቢዎች ጦርነት ተከፍቷል። ባንቱዊ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጽህፈት ቤት የሚገኝበት ሲሆን፣ በርከታ የዲንቃ ተወላጆች በጽህፈት ቤቱ ግቢ ውስጥ መግባታቸው ታውቋል። በጁባ የኑዌር ተወላጆች ከዲንቃ ጎሳዎች ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል ብለው በተመድ ጽ/ቤት ውስጥ ሲጠለሉ፣ በቤንቲዩ ደግሞ በተቃራኒው ዲንቃዎች ተጠልለዋል።
ፕሬዚዳንት ኦባማ አዲሲቷ አገር ወደ እርስ በርስ ጦርነት ልትገባ እንደምትችል አስጠንቅቀዋል። እስካሁን ባለው አሀዝ ከ500 ያላነሱ ሰዎች ተገድለዋል።

Thursday, December 19, 2013
ከወያኔ ክፋትና እብሪት እንጂ ፍትህ አይጠበቅም
http://www.ginbot7.org
ወያኔ ባለፉት ሃያ ሁለት አመታት የአገራችንን የፍትህ ተቋሞች አንዴ አንደ ቂም መበቀያ ሌላ ግዜ ደግሞ እንደ ማጥቂያ መሳሪያ እየተጠቀመባቸዉ የፖለቲካ ተቀናቃኞቹንና ጥርስ የነከሰባቸዉን የህብረተሰብ አባላት እያሰረ፤ እያሳደደና እየገደለ ከርሞ ዛሬ ላይ ደርሷል። በተለይ ከግንቦት 1997ቱ ምርጫ በኋላ ወያኔ ብዕርና ወረቀት ይዘዉ በሃሳብና በአመክኖ የታገሉትን ሰላማዊ ዜጎች “ሽብርተኞች”፤ ድምጻችን ይሰማ ብለዉ የመብትና የነጻነት ጥያቄ አንግበዉ በሰላማዊ መንገድ የታገሉትን ኢትዮጵያዉያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ደግሞ “አክራሪዎች” እያለ ፍርድ ቤት በማቅረብ በፍትህ ተቋሞች በኩል የፖለቲካ ዉሳኔ በማሳለፍ ሠላማዊ ዜጎችን ለረጂም ግዜ እስርና እንግልት ዳርጓል።
ወያኔ ለኢትዮጵያና ለዜጎቿ ደንታ የሌለዉ እና ከስህተቱ የማይማር የግብዞችና የዘረኞች ስብስብ ስለሆነ አሁንም የአገሪቱን የፍትህ ተቋሞች እንደ ማጥቂያ መሳሪያ እየተጠቀመ የኢትዮጵያን ህዝብ በፍርሃት ጨለማ ዉስጥ ሸብቦ እየገዛ ለመኖር የቆረጠ ይመስላል። ባለፈዉ ሳምንት አጋማሽ ላይ የወያኔ አገዛዝ ከአንድ አመት ተኩል በላይ እስር ቤት ዉስጥ አጉሮ ያቆያቸዉን የድምጻችን ይሰማ መሪዎች ከፊሎቹን በነፃ ተለቅቀዋል የሚል ከፊሎቹን ደግሞ ተከላከሉ የሚል ትርጉም የለሽ ብይን ሰጥቷል። በህወሀት ታጋዮች የተሞላዉ ፍርደ ገምድሉ የወያኔ ፍርድ ቤት እንኳን ተከሳሾቹ በተከሰሱበት ሽብር የመፈጸም ወንጀል ምንም አይነት ማስረጃ አልተገኘባቸዉም ሲል አገዛዙ ግን የፖለቲካ ክንዱን በመጠቀም ማስረጃ ያልተገኘባቸዉን ሠላማዊ ዜጎች የተከሰሱበትን መሰረተ ቢስ ክስ ተከላከሉ የሚል የፖለቲካ ዉሳኔ ሰጥቷል።
የወያኔ አገዛዝ የሙስሊሙን ህብረተሰብ የመፍትሄ አፈላላጊ ቡድን መሪዎች ፍርድ ቤት ያቀረባቸዉ ለምዕራባዉያን ለጋሾቹና ለአለም አቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ዉስጥ ፍትህ ያለ ለማስመሰል ነዉ እንጂ ወያኔ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን የፈረደባቸዉ ያሰራቸዉ ቀን ነዉ። የወያኔ የፍትህ ታሪክ በግልጽ እንደሚያሳየን ወያኔ ግለሰቦችን የሚያስረዉ ለክስ የሚያበቃ ማስረጃ አግኝቶባቸዉ አይደለም፤ ይልቁንም ወያኔ ማስረጃዎችን እየፈበረከ ለፍረድ ቤቶች የሚያቀርበዉ ግለሰቦችን ካሰረና ሰብዓዊ መብታቸዉን ከገፈፈ በኋላ ነዉ። ለምሳሌ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን አስሮ ብዙም ሳይቆይ የእነዚህን ሰላማዊ ዜጎች ተክለ ሰዉነት ጥላሸት የቀባና ግለሰቦቹን ያለ ማስረጃ ወንጀለኛ አድርጎ የፈረጀዉን “ጂሐዳዊ ሀረካት” የሚል የፈጠራ ድራማ ሰርቶ ለህዝብ አቅርቧል።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሽብር በመፈጸም ወንጀል ተጠርጥረዉ የቀረቡለትን ግለሰቦች በተከሰሱበት ወንጀል ማስረጃ አላገኘሁባቸዉም ካለ በኋላ ሁሉንም በነጻ አለማሰናበቱ የሚያሳየን የወያኔ ፍርድ ቤቶች ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነጻ አለመሆናቸዉን ብቻ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያ ዉስጥ ፍርድ ቤቶች የገዢዉ ፓርቲ የማጥቂያ መሳሪያዎች መሆናቸዉን ጭምር ነዉ። የወያኔን አገዛዝ ከሌሎች አምባገነኖች ለይቶ አደገኛ የሚያደርገዉና በምዕራባዉያን መንግስታትና በቀላጤዎቻቸዉ እንዲወደስ ያደረገዉም ይሄዉ አገዛዙ የሚቃወሙትን ኃይሎች የሚያጠፋቸዉ እንደሌሎቹ አምባገነኖች በግልጽ ሳይሆን በህግ ሽፋን ዉስጥ በስዉር መሆኑ ነዉ።
የወያኔዉ ፍርድ ቤት በተመሳሳይ ወንጀል ተከስሰዉ የቀረቡለትን ነገር ግን ምንም መረጃ ያላገኘባቸዉን የድምጻችን ይሰማ መሪዎች ገሚሶቹን በነፃ ለቅቆ የተቀሩትን ጥፋተኛ አለመሆናችሁን አረጋግጡ ብሎ መወሰኑ የወያኔን ሁለት እኩይ አላማዎች ያሳየናል። የመጀመሪያዉ የወያኔ አላማ በአላማቸዉ ጸንተዉ የቆሙትን የድምጻችን ይሰማ መሪዎች መከፋፈል ሲሆን፤ ሁለተኛ አላማዉ ደግሞ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የቀረቡላቸዉን የክስ መዝገቦች በሚገባ አጣርተዉ ዉሳኔ የሚሰጡ መሆናቸዉን ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ ለማሳየት ነዉ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ግን እንደዚህ አይነቶቹን የወያኔ እኩይ ተግባሮች ካወቀ ዉሎ አድሯል፤ ስለሆነም ከወያኔ ፍትህ ጠብቆ አያዉቅም፤ ወያኔ የክፋትና የበቀል ምንጭ ነዉና ለደፊትም አይጠብቅም። የድምጻችን ይሰማ መሪዎችም ሆኑ ከእነሱ በፊት በግፍ ታስረዉ መከራቸዉን የሚያዩት የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፤ ጋዜጠኞችና የሲቪክ ማህበራት መሪዎች የታሰሩት ለቆሙለት የፍትህ፤ የነጻነትና የእኩልነት አላማ እንደ አለት ጸንተዉ በመቆማቸዉ ነዉ። እነዚህ ጀግኖች የታሰሩለት አላማ የሁላችንም አላማ ነዉና ፍትህ፤ እኩልነትና ነጻነት የጠማን ኢትዮጵያዉያን ክንዳችንን አስተባብረን የችግሮቻችን ሁሉ ምንጭ በሆነዉ በወያኔ ስርዐት ላይ ክንዳችንን በጋራ እናንሳ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
POSTED BY SAMUALE TEWELDE

Subscribe to:
Posts (Atom)